Loading...

Loading

Loading
(You are in the browser Reader mode)

ክፍል 1—እግዚአብሔር ለወጣቶች ያለው ዓላማ

ሥራው በሁሉም ዘርፍ ወደ ፊት እንዲቀጥል እግዚአብሔር የወጣትነት ብርታትን፣ ቅንአትንና ድፍረትን ይፈልጋል:: ሥራው ወደ ፊት እንዲቀጥል እንዲረዱ ወጣቶችን መርጦአቸዋል:: በጠራ አእምሮ ማቀድና በደፋር እጆች መስራት ትኩስና ያልደከመ ጉልበት ይሻል:: ወጣት ወንዶችና ሴቶች ያላቸውን ኃይል ሥራ ላይ በማዋል በተስተካከለ አስተሳሰብና ብርቱ ተግባር ለእርሱ ክብርና ለመሰሎቻቸው ደህንነትን ለማስገኘት የወጣትነት ብርታታቸውን ለእግዚአብሔር እንዲሰጡ ተጋብዘዋል:: Gospel Workers pp. 67. MYPAmh 21.1